Home

"በራሱ ሃሳብ ላይ የቆመ ማህበረሰብን እንፍጠር"

ማኅበረ ሰብዓዊያን

የማህበሩ ዓላማ

የሰው ልጅ ልዕለ ኃያል በሆነ ሃሳብ ከፍተኛ ደረጃ እንዲደርስ እና በሌሎች ሃሳቦች ጥገኛ እንዳይሆን፣ ይልቁንም ተፈጥሮአዊ ነጻነቱን ጠብቆ የሚገጥሙትን ተግዳሮቶች ማለፍ እንዲችል የሚያግዙ የጥበብ ሃሳቦች ላይ የሚሰራ መንግስታዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ሃይማኖታዊ ወይም ወገናዊ ያልሆነ ድርጅት ነው።
የማህበረ ሰብዓዊያን መስራች አባላት - 2013 ዓ.ም
የማህበረ ሰብዓዊያን መስራች አባላት - 2013 ዓ.ም

ስለ ድርጅታችን

ማኅበረ ሰብዓዊያን በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ተመዝግቦ በ2013 ዓ.ም ተመስርቷል። የድርጅቱ ዓላማ ማንኛውም ዓይነት የልዩነት ምክንያት ሳያግዳቸው በከፍተኛ ልዕልና ላይ የሚገኙ ሃሳቦች (ጥበቦች) ወደ ተግባር የሚለወጡበትና ጥቅም ላይ የሚውሉበትን ሥርዓት እንዲዘረጋ የሚያስችል የሰው ኃይል ማዕቀፍ በመዘርጋት በራሱ ሃሳብ ላይ የቆመ ማኅበረሰብ እንዲፈጠር አስቻይ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎች

ከተቋማት ጋር ስምምነት መፈጸም በጋራ መስራት

ማኅበረ ሰብዓዊያን ዓላማውን ዓላማቸው ካደረጉ ልዩ ተሰጥኦ ካላቸው ግለሰቦች ወይም ለሰው ልጆች ጠቃሚ ስራዎችን ከሚሰሩ ተቋማት ጋር ስምምነት በመፍጠር ሃሳቦቻቸው ለብዙሃን የሚደርስበትን የትብብር ማዕቀፎችን በመፍጠር በጋራ ይሠራል።

ማኅበሩ የዳበረ የሃሳብ፣ የዕውቀትና የልምድ ባለቤቶች የሆኑ አባላቱን በማስተባበር ወጥነት ያለው ፕሮፌሽናል የስልጠና ፕሮግራም እንዲቀርፁና ስልጠናዎቹንም በኮርስ መልክ እንዲዳረስ የማድረግ ሥራዎችን ይሰራል፡፡ በዚህ መልኩ በእስካሁኑ ሂደት በማህበሩ የፕሮግራም ማስተባበሪያና የስልጠና ማዕከል ውስጥ የማኅበሩ አባል የሆኑ አሳቢያንን፣ ተመራማሪዎችን፣ ደራሲያንንና ሰዓሊያን ሃሳቦቻቸውን እና ክህሎቶቻቸውን የሚያጋሩባቸው መድረኮች ተዘጋጅተዋል።

ሚዲያ የሰውን ልጅ የአስተሳሰብ አቅጣጫና ፍላጎት የሚወስን ትልቅ ተፅዕኖ ፈጣሪ ኃይል በመሆኑ ይህንን ኃይል በኢትዮጵያ ውስጥ በተሻለ ጥበብና ይዘት ለመጠቀም በማሰብ የማህበሩ መስራቾች “መልክአ-ሃሳብ” የተባለ የሚድያ ፕሮግራም መስርተዋል፡፡ ለሶስት አመታት በአሃዱ ሬዱዮ እና በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሲተላለፍ የቆየው የ“መልክአ-ሃሳብ” ፕሮግራም የአስተሳሰብ ዕይታዎች እንዲሰፉ እና ትውልዱ በራሱ የሃሳብ መሰረት ላይ ፀንቶ እንዲቆም የሚያስችሉ ርዕሰ-ሃሳቦችን ሲያዘጋጅ ቆይቷል፡፡ በቀጣይ ሂደትም ወደ ቴሌቪዝን የስርጭት ፕሮግራም ለማሳደግ ታቅዷል።

ማኅበሩ ከአዲስ አበባ ከተማ በ40 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ የሚገኘውን የኤረር ተራራ ጥብቅ ደንና በደኑ ውስጥ የሚገኘውን የቱሪስት ማረፊያ ግቢ እና ተፈጥሯዊ አካባቢውን የማይስ ቱሪዝም (M.I.C.E. Tourism) መዳረሻ በማድረግ የሰራው ስራ አንዱ ቢሆንም ለወደፊትም ተጨማሪ ስፍራዎችን የማመቻቸት ስራዎች ይቀጥላሉ።

ከማህበሩ ጋር እየሰሩ የሚገኙ ተቋማት

ከማህበረ ሰብዓዊያን ዓላማ ጋር አብረው በመቆም የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እያደረጉ የሚገኙ ተቋማት ዝርዝር

addmesh books
photo 2025 11 07 15 20 39
photo 2025 11 07 15 20 41
አድሜሽ | Addmesh
ጤንነት ሰጠኝ ወይም (ወ/ሩፋኤል) ከጥበብ ዘንድ የተማረውን ሃሳብ ለሰው ልጆች ይጠቅማል በማለት በመጽሐፍት እና በትንታኔዎች በአድሜሽ መጽሐፍት ንግድ ስራ አማካኘት በተለያዩ መንገዶች እያቀረበ ይገኛል። እነዚህን ሃሳቦችም በራሱ ድረ ገጽ ላይ ያቀርባል በተጨማሪም በአካል ለሚሳተፉ ተሳታፊዎች ከማህበረ ሰብዓዊያን ጋር በመተባበር በማህበረ ሰብዓዊያን አዳራሽ በአካል እና በኦንላይን ስርጭት ያቀርባል።
አድራሻ
📩 ድረ ገጽ | Website: www.addmeshbook.com
📩 ኢሜይል | Email: addmeshms@gmail.com
🔗 ፌስቡክ | Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=61562926796941&mibextid=LQQJ4d&rdid=HgfKaTl8sHjEB1b7
🔗 እንስታግራም | Instagram: https://www.instagram.com/addmeshmedi/
🔗 ቴሌግራም | Telegram: https://t.me/addmeshbook
📞 ስልክ | Phone:+251 911 729 553
img 2179.0b2f435b6ed34d3ea81a
img 2177.abb674c80509865b9741
img 2146.9f7e144bb3d3e388a2ce
img 1988.38669d97a38fe2deeaa7
img 7.9ea14244b258df251278
img 6.5f0421fadbebeadb66ad
ከአ-ጥበባት | Ke’A Tibebat
ክአ-ጥበባት ኢትዮጵያዊ መሰረት ያላቸው የእደ-ጥበብ ውጠቶችን ማለትም እንደ ለጤና  መጠበቂያ የሚሆኑ ተፈጥሯዊ ይዘታቸውን ጠብቀው የተዘጋጁ የእጽዋት ውጤቶች ፣ ለተለያዩ ጌጣጌጥነት እና የእለተ እለት መገልገያ የሆኑ የቆዳ እና የሸክላ ውጤቶችን፣ በማምረት ለሀገር ውስጥ እና ለውጪ ገበያ ለማውቅረብ የተቋቋመ ድርጅት ነው።
አድራሻ
📩 ድረ ገጽ | Website: www.keatibebat.com
📩 ኢሜይል | Email: keatibebat@gmail.com
📣 ቴሌግራም | Telegram: https://t.me/keatibebat
📞 ስልክ | Phone: +251 90 407 4047
one voice academy psd 1
564606366 24873882458898569 6527612882289969394 n
poster
564210932 1118600683722839 505004581186781623 n
ዋን ቮይስ አካዳሚ | One Voice Academy
የዋን ቮይስ ዋና ተግባር የኢትዮጵያ ሙዚቃ በዓለም አቀፍ ደረጃ ጎልቶ ወደ ከፍታ የሚወጣበትን መንገድ ማመቻቸት ሲሆን ከዚህ ጋር ተያይዞም የድምጽ ስልጠናዎችን በመስጠት የሙዚቃው ኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ የበኩሉን አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ ይገኛል።
አድራሻ
📩 ኢሜይል | Email፡ onevoicesound13@gmail.com
📺 ዩቲዩብ | YouTube: https://youtube.com/@onevoicesound
🔗 ፌስቡክ | Facebook: https://facebook.com/Onevoicesound
🔗 ኢንስታግራም | Instagram: https://www.instagram.com/onevoice_sound
🔗 ቲክቶክ | TikTok: www.tiktok.com/@onevoice134
📞 ስልክ | Phone: +251 919 890 486
photo 2026 01 12 15 29 45 (4)
pottery 1
pottery 2
pottery 3
pottery 4
ሮሃ ሸክላ | Roha Pottery
ለተለያዩ መገልገያ እና ለጌጣጌጥነት የሚያገለግሉ የሸክላ ውጤቶችን ተፈጥሯዊ ይዘትና ቀለሙን በጠበቀ መልኩ የሚያመርትና የሚያቀርብ ድርጅት ሲሆን የሸክላ አሰራር ስልጠናዎችን ይሰጣል። 
አድራሻ
🔗 ፌስቡክ | Facebook: https://www.facebook.com/share/19p1yABbnc/
🔗 ኢንስታግራም | Instagram: https://www.threads.com/@rohapottery_134712
🔗 ቴሌግራም | Telegram: https://t.me/Rohapottery_134712
🔗 ቲክቶክ | TikTok: https://www.tiktok.com/@rohapottery?_r=1&_t=ZM-91750gs3SP6
📞 ስልክ | Phone: +251 919 890 486
gift packaging
office desk
tray
wallet
ወዓ | We’A
የቆዳ ውጠቶቻችን በእደ ጥበብ ባለሙያ እጆች የተሠሩ እና ዲዛይናቸውም በአብዛኛው ኢትዮጵያዊ የጥበብ ፓተርኖች ላይ ትኩረት ያደረጉ ናቸው።ለኮርፖሬት ኢንዱስትሪዎች እና ለኩባንያ ብራንዶች የስጦታ መያዣዎችን፣ ዋሌቶችን ወዘተ እንሰራለን፤ ይህም በገበያው ላይ ተወዳጅና ተፈላጊ እንድንሆን አድርጎናል።

አድራሻ
🔗 ፌስቡክ | Facebook: https://www.facebook.com/share/19p1yABbnc/
🔗 ኢንስታግራም | Instagram: https://www.threads.com/@rohapottery_134712
🔗 ቴሌግራም | Telegram: https://t.me/Rohapottery_134712
🔗 ቲክቶክ | TikTok: https://www.tiktok.com/@rohapottery?_r=1&_t=ZM-91750gs3SP6
📞 ስልክ | Phone: +251 919 890 486

የአባላት ስብጥር

ማኅበሩ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ውስጥ የሚሠሩ ፕሮፌሽናል ሙያተኞችን፣ ደራሲያንን፣ ተመራማሪዎችን፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት ውስጥ በተለያየ የኃላፊነት እርከን ላይ የሚሰሩ ግለሰቦችን፣ በግሉ ዘርፍ የሚሰሩ ሥራ ፈጣሪዎችን፣ ተማሪዎችንና ሌሎችንም በአባልነት አቅፎ ይዟል፡፡

ምንም እንኳ የማህበሩ መሠረት ኢትዮጵያ ውስጥ ቢሆንም በሃገራዊና በፖለቲካዊ ማዕቀፎች የተገደበ ባለመሆኑ ዜግነታቸው ኢትዮጵያዊ ያልሆኑትን ጨምሮ አሁን ላይ በአፍሪካ፣ በሰሜን አሜሪካ እና በአውሮፓ አህጉራት የሚገኙ አባላት አሉት። ከዚህ በተጨማሪም ማህበሩ የተለያዩ እምነቶችን የሚከተሉ አባላትን በውስጡ አካቷል። ስለዚህ ባጠቃላይ ይህ የሚያሳየው ማህበሩ ሁሉንም የሰው ልጆች ለማቀፍ የሚችል ሃሳብ ይዞ የቆመ መሆኑን ነው።

አባል ለመሆን ያነጋግሩን

Scroll to Top