Members

አባል ለመሆን ማድረግ ያለብዎ...

የሚከተሉትን ሦስት ነገሮችን በመተግበር አባል መሆን ይችላሉ!

01

ቀጠሮ መያዝ

አባል ለመሆን በመጀመሪያ ከድርጅቱ ሰራተኞች ጋር የገጽለገጽ ቃለመጠይቅ (Interview) ለማድረግ ቀጠሮ መያዝ ያስፈልጋል፣

02

ቃለመጠይቅ ማድረግ

በያዙት ቀጠሮ መሰረት የ10 ደቂቃ የገጽለገጽ ቃለመጠይቅ (Interview) ክፍለጊዜ ይኖራል። ከዚያም በ3 የስራ ቀናት ውስጥ የአባልነት ጥያቄዎ ተቀባይነት ማግኘቱ ተደውሎ አልያም በሌላ መንገድ ይነገርዎታል፣

03

ምዝገባ ማድረግ

የአባልነት ጥያቄዎ ተቀባይነት ማግኘቱን ተከትሎ በኢሜይል አድራሻዎ ወይም በሌላ መንገድ የምዝገባ ፎርም ይላክልዎታል። ከዚያም የምዝገባ ክፍያን ይከፍላሉ፣ በመቀጠልም የአባልነት ፎርሙን ይሞላሉ፣

አባል ለመሆን ያነጋግሩን

ስለ አባልነት

የድርጅቱ አባል ለመሆን በድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብ ላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟላ እና በመተዳደሪያ ደንቡም መሠረት በቦርድ ውሳኔ ተቀባይነት ማግኘትን ይጠይቃል።

አባል ለመሆን የሚከተሉትን ሦስት ደረጃዎች ይከተላሉ
1. የአባልነት ጥያቄ ማመልከቻ (Application Form) በመሙላት ቀጠሮ ማስያዝ
2. ባስያዙት ቀጠሮ መሰረት ከድርጅቱ ሰራተኞች ጋር የ10 ደቂቃ የገጽለገጽ ቃለመጠይቅ (Interview) ክፍለጊዜ ይኖራል። ከዚያም በ3 የስራ ቀናት ውስጥ የአባልነት ጥያቄዎ ተቀባይነት ማግኘቱ ተደውሎ አልያም በሌላ መንገድ ይነገርዎታል።
3. የአባልነት ጥያቄዎ ተገባይነት ማግኘቱን ተከትሎ የምዝገባ ክፍያን ይከፍላሉ፣ በመቀጠልም የአባልነት ፎርም ይሞላሉ።

ተጨማሪ መረጃዎች

የአባልነት መስፈርቶች

- በድርጅቱ ዓላማና ግብ የሚያምን
- እድሜው 18 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ
- የድርጅቱን የመተዳደሪያ ደንብ እና በቦርዱ በየጊዜው የሚወጡ ደንቦችና መመሪያዎችን የሚቀበልና ተግባራዊ የሚያደርግ
- በቦርዱ ውሳኔ ያገኙ ክፍያዎችንና መዋጮዎችን መክፈል የሚችል መደበኛ አባል ለመሆን ያቀረበው ጥያቄ በቦርድ ውሳኔ ማግኘት የቻለ

- አባላት በፈቃደኝነት ለማህበሩ ገንዘብ ገቢ በማድረግ ድጋፍ ማድረግ ይችላሉ
- አባላት በፈቃደኘነት በቁሳቁስ ማህበሩን መደገፍ ይችላሉ
- አባላት እንደየተሰጥኦዋቸው ማህበሩ ክህሎታቸውን በሚፈልግባቸው ቦታዎች ላይ በነጻ ማገልገል ይችላሉ። ለምሳሌ(በዝግግጅት አስተባባሪነት፣ የሂሳብ ሙያ፣ ልዩ ልዩ የእጅ ሙያዎች ወዘተ...)
- የድርጅቱ አባልነት ለወራሾችም ሆነ ለሌላ ሰው የማይተላለፍ የግል መብት ነው።
- ለድርጅቱ ዓላማና ተልዕኮዎች መሳካት የሚጠቅሙ ስራዎችን ማከናወን
- ስለድርጅቱ እንቅስቃሴ ማንኛውንም መረጃ ጠይቆ ማግኘት
- በቦርዱ በሚጠራው የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ላይ የመገኘትና ስለድርጅቱ እንቅስቃሴ አስተያየትና ድምጽ መስጠት
- በፈለገ ጊዜ ከድርጅቱ የመውጣት ወይም መሰረዝ

ስለ የምዝገባ እና ወርሃዊ ክያዎች:
- የአባልነት መመዝገቢያ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ነው።
- አባላት በየወሩ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) የአባልነት ወርሃዊ ክፍያ ይከፍላሉ

የማህበረ ሰብዓዊያን አካውንቶች:
- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE): 1000346839329
- አቢሲኒያ ባንክ (BOA): 42498963
- አዋሽ ባንክ (Awash Bank): 013086588304300

ማስታወሻ፡
* የወርሃዊ ክፍያ በኢትዮጵያ ቀን አቆጣጠር ወሩ በገባ ከ 1 - 7 ቀናት ባሉት ውስጥ መክፈል ይኖርበታል። ለምሳሌ የህዳር ወር ክፍያ የመክፈያ ጊዜ ከህዳር 1 እስከ ህዳር 7 ነው። ይህም ማለት ከህዳር 7 በኋላ ክፍያ ቢፈጽሙ አዘግይተው እንደከፈሉ ይቆጠራል። ከተቻለም ወሩ ከመግባቱ አስቀድሞ መክፈል ይቻላል።
* የወደፊት ወርሃዊ ክፍያዎችን ከአንድ ወር ላይ የተፈለገውን ያህል ወራት መክፈል ይቻላል። ለምሳሌ የ3 ወራት የ1 ዓመት ወዘተ...
* ክፍያ ከፈጸሙ በኋላ ቴሌግራም ላይ በስልክ ቁጥር +251974082183 ወይም በኢሜይል mahberesebawiyan@gmail.com ላይ የከፈሉበትን ደረሰኝ ስክሪን ሻት ከስምዎ ጋር ጽፈው ቢልኩልን የከፋዩን ስም ለመለየት ይረዳናል።
* በሞባይል ባንኪንግ ተጠቅመው ሲከፍሉ ከእርስዎ ሌላ ለሌላ የማህበሩ አባል እየከፈሉ እንደሆነ Reason የሚለው ቦታ ላይ የከፈሉለትን አባል / አባላት ስም ይጻፉ።

- ወርሃዊ መዋጮዎች እና ሌሎች ክፍያዎች እንደአስፈላጊነቱ በመመሪያ የሚወሰኑ መሆናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ከስድስት ወራት በላይ ያለበቂ ምክንያት ወርሃዊ መዋጮ ያልከፈለ አባል እንደ ምክንያቱ በገንዘብ መቀጮ በአዘገየበት ወር ብር 50 (ሃምሳ ብር) እንዲከፍል ይደረጋል። በማንኛውም ምክንያት ወርሃዊ ክፍያን ለአንድ ዓመት ያህል ያልከፈለ መደበኛ አባል ከአባልነት እንዲሰረዝ በቦርዱ ይወሰናል። ወራት ያለበቂ ምክንያት ወርሃዊ ክፍያ ያልከፈለ አባል ምክር ተሰጦት የአባልነት ክፍያውን እንዲከፍል ይደረጋል።

- የድርጅቱን ክብርና ህልውና በሚነካ ወይም በሚያናጋ ተግባር ላይ መሳተፉ በማስረጃ ሲረጋገጥና ይህም በቦርድ ውሳኔ ሲያገኝ
- ለድርጅቱ ዓላማ መሳካት በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ተገቢውን ተሳትፎ ለማድረግ ፈቃደኛ ሳይሆን ሲቀር እና ይህም በቦርድ ሲረጋገጥ
- መተዳደሪያ ደንቡ ላይ በተገለጸው መሠርተ ወይም በሌላ አጥጋቢ ምክንያት ከአባልነት እንዲሰናበት በቦርድ ሲወሰን - ወርሃዊ መዋጮውን ለአንድ ዓመት ያህል ጊዜ ባለመክፈሉ ምክንያት
- ከድርጅቱ አባልነት በራሱ ፈቃድ ለመልቀቅ በጽሑፍ ሲጠይቅ

Scroll to Top